ቀጥታ፡

ባርሴሎና አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ12ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ባርሴሎና አትሌቲኮ ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጁሊያኖ ሲሚዮኒ በ10ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል አትሌቲኮ ማድሪድን መሪ አድርጓል።


ፌርሚን ሎፔዝ በ45ኛው እና በ66ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፋቸው ግቦች ባርሴሎና አሸናፊ ሆኗል።

በጨዋታው ባርሴሎና አንጻራዊ ሊባል የሚችል ብልጫ ወስዷል።


በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ባርሴሎና በ33 ነጥብ የሊግ መሪነቱን አጠናክሯል።

በአንጻሩ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አትሌቲኮ ማድሪድ በ28 ነጥብ ከነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ዝቅ ብሏል።

ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች በኋላ በ13ኛ ሳምንት አትሌቲኮ ማድሪድ ከጌታፌ፣ ባርሴሎና ከቪያሪያል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም