ቀጥታ፡

በተጠባቂው መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 ረትቷል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምህረት አየለ እና እሙሽ ዳንኤል ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የወቅቱ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘጠኝ ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ4 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች አምና እስከ መጨረሻው ሳምንት የዋንጫ ተፎካካሪ ነበሩ።

በሌሎች መርሐ ግብሮች መቻል ድሬዳዋ ከተማን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።


አዳማ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1፣ ባህር ዳር ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከልን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

ሀዋሳ ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ እና ልደታ ክፍለ ከተማ ከሸገር ከተማ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ ሶስተኛ ሳምንት ፍጻሜውን አግኝቷል።

የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ህዳር 5 እና 6 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም