ማንችስተር ዩናይትድ እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና አስቶንቪላ ያደረጉት ጨዋታ አራት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በኦልትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በፍጹም ቅጣት ምት፣ ዩሪ ቲሊማንስ፣ጆሹዋ ዚርኪዜ እና ፓትሪክ ዶርጉ የዩናይትድን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አሊሰን ኤድዋርድ፣ ኒኮላስ ጃክሰን፣ ጆን ማጊን (ፍጹም ቅጣት ምት) እና ሊዮን ጎሬትዝካ ለአስቶንቪላ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ዚርኪዜና ዶርጉ በባከኑ ደቂቃዎች ያስቆጠሯቸው ጎሎች ዩናይትድን አቻ አድርገዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በስምንት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ባለፉት ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ዩናይትድ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።
ወራጅ ቀጠና ሲገባም ከ40 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አስቶንቪላ በ13 ነጥብ 10ተኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረጉ ሌሎች መርሐ ግብሮች ሊቨርፑል ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 ሲረታ ቼልሲ በሰንደርላንድ የ1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
ብራይተን ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 እና ቦርንማውዝ ኤፕስዊች ታውንን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ 10ኛ ሳምንት የተጠናቀቀ ሲሆን ፕሪሚየር ሊጉ በብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ምክንያት ይቋረጣል።
ሊጉ ህዳር 12 2019 ዓ.ም በ11ኛ ሳምንት ይመለሳል።