ቀጥታ፡

ሊቨርፑል ክሪስታል ፓላስን ሲያሸንፍ ቼልሲ በሰንደርላንድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፦  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ዛሬ ባደረገው የሊግ መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችሏል።

በጨዋታው የሊቨርፑልን የድል ግቦች ማክ አሊስተር፣ አሌክሳንደር አይሳክ እና ፍሎሪያን ቨርትዝ አስቆጥረዋል።

በሌላ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል።

በተመሳሳይ ብራይተን ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 በማሸነፍ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

በሌላ ጨዋታ በርንማውዝ ኢፕስዊች ታውንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሙሉ ሦስት ነጥብ ወስዷል።

በውጤቶቹ መሠረት በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ብራይተን በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፣ ሊቨርፑል በ18 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።ቼልሲ በበኩሉ በ16 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም