ቀጥታ፡

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኮፕ-31 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ቱርክዬ አንታሊያ ገቡ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ-32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኮፕ-31 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ቱርክዬ አንታሊያ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኮፕ-31 ፕሬዝዳንት፣ ከተለያዩ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪ ቡድኖችና ከአጋር አካላት ጋር ይወያያሉ፡፡


 

ውይይቶቹ ከኮፕ-31 ወደ ኮፕ-32 የሚደረገውን ሽግግር በተሳለጠ ሁኔታ ለማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ኮፕ-32 አካታች፣ በተግባር ላይ ያተኮረና ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆን የጋራ መግባባትንና ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም