ቀጥታ፡

የብልፅግና ፓርቲ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ) ፦የብልፅግና ፓርቲ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤትና የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በግምገማው የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ  የሥራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በብልፅግና ፓርቲ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር  ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። 

በውይይቱም በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ የሥራ አቅጣጫዎች በጥልቀት ተመልክተዋል።

በመድረኩ የሥራ አፈጻጸሙ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ተለይተው ተገምግመዋል። 

በተጨማሪም የተገኙ ልምዶችን ማጠናከር፣ የአፈጻጸም ክፍተቶችን ማረም እና ቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ውጤታማነት ለመፈጸም በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ የቀጣይ የሥራ አፈጻጸምን ለማጠናከር ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ መስጠታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም