ልደታ ክፍለ ከተማ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ልደታ ክፍለ ከተማ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ልደታ ክፍለ ከተማ እና ሸገር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምህረት ቶንጆ በ48ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ጎል ሸገር ከተማ መሪ ሆኗል።
ብሩክታዊት አየለ በ87ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ጎል ልደታ ክፍለ ከተማን አቻ አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በሶስት ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ከፍ አድርጓል።
ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ማሸነፍ አልቻለም።
ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ ከአራተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ከፍ ብሏል።