ማንችስተር ሲቲ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት ማንችስተር ሲቲን 3 ለ 1 ረትቷል።
ማምሻውን በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊያም ዴላፕ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጃር ኩንያ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ራያን ቼርኪ የሲቲን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
ማንችስተር ሲቲ በጨዋታው የወሰደውን የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በሚገባ ወደ ግብ እድሎች መቀየር አልቻለም።
ባለሜዳው ፎረስት ያገኛቸውን የግብ እድሎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ተጠቅሟል።
በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈት ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ በ21 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ነጥብ ከፍ ብሏል።
ከአምስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኖቲንግሃም ፎረስት በዘጠኝ ነጥብ ከነበረበት 19ኛ ደረጃ ወደ 16ኛ ከፍ በማለት ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በ11ኛ ሳምንት ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንማውዝ፣ ማንችስተር ሲቲ ከፉልሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።