ቀጥታ፡

የሶስተኛው ዙር ኮሪደር ልማት በውስጡ ምን አካቷል...!

1. ከጎሮ–ኮዬ ፈጬ እስከ ቱሉ ዲምቱ የሚዘልቀው የኮሪደር ልማት፣ እና

2. ከካራ–ቦሌ አየር ማረፊያ መንገድ በጎሮ እስከ አቃቂ የሚዘልቀው 22 ኪ.ሜ. የወንዝ ዳርቻ ልማት ፤

👉 የመንገድ ልማት፦

* ከጎሮ–ኮዬ ፈጬ–ቱሉ ዲምቱ 15 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው መንገድ ነው።

* የመንገዱ ስፋት 114 ሜትር ነው።

* በአንድ ጊዜ 8 ተሽከርካሪዎችን ያስተናግዳል።

* ሰፋፊ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች ሥራን ያካትታል።


 

👉 የአረንጓዴ ልማት፦

* በ30 ሜትር ስፋት የሚዘረጋ፣ 70 ሄክታር መሬትን የሚሸፍን የመንገድ ዳር የአረንጓዴ ልማት ሥራን ያካትታል።

👉 የውኃና የፍሳሽ ልማት፦

* በ12 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ በቀን 106 ሺህ ሜትር ኪዩብ የመጠጥ ውኃ ለማምረት የሚያስችል ሥራን ያካትታል።

* የፍሳሽ ውኃ ማጣሪያ ጣቢያ ተገንብቷል።

* 206 ኪ.ሜ. የፍሳሽ መስመር ሥራን ያካትታል።

👉 የወንዝ ዳርቻ ልማት፦

* ከካራ–ቦሌ አየር ማረፊያ መንገድ በጎሮ እስከ አቃቂ የሚዘልቀው 22 ኪ.ሜ. የወንዝ ዳርቻ ልማት ፣ 11.2 ሄክታር የአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ ነው።

* 324 ሄክታር የሚሆን መሬትን የሚሸፍን የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ሥራ ወንዙን ተከትሎ እየተከናወነ ይገኛል።

* 4,100 ሜትር ኪዩብ የጋቢዮን ሥራ እየተሰራ ነው።


 

* 1,500 ሜትር ኪዩብ የእርከን ሥራን ያካትታል።

⁠በአጠቃላይ ስራው እየተፋጠነ ስለሆነ በአካባቢው ቅድሚያ የማልማት መብት ያገኛችሁ የግል አልሚዎችም እድታፋጥኑ እናሳስባለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም