ቀጥታ፡

አርሰናል ሁል ሲቲን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ሁል ሲቲን 1 ለ 0 ረትቷል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ በ72ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

ባለሜዳው አርሰናል በጨዋታው ከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ ወስዷል።

አርሰናል በ27 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ከፍ አድርጓል።

ሁል ሲቲ በ11 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ፉልሃም እና ኒውካስትል ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ኖቲንግሃም ፎረስት ከማንችስተር ሲቲ በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም