ቀጥታ፡

የሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች በተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019(ኢዜአ)፦ የሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

በጉብኙቱ የአፍሪካ አስተዳደር ማዕከል ሊቀ መንበር ቤኔዲክታ ላሲ እና የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢኒሼቲቭ አዲስ አመራሮችን ጨምሮ የጉባዔው ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል።

የጉባዔው ተሳታፊዎች የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤትን፣ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን እንዲሁም የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

ከጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ «ዕድገትን መምራት፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ መጻኢ ኢኮኖሚ መሐንዲሶች እንደ መሆናቸው» በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ማምሻውን ተጠናቋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም