ቀጥታ፡

ሊድስ ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 1 ለ 0 ረትቷል።

በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኖሃ ኦካፎር በ79ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊድስ ዩናይትድ በ14 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ12 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ11ኛ ሳምንት ሊድስ ዩናይትድ ከቼልሲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከኤፕስዊች ታውን ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም