ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ከሁል ሲቲ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም ሁል ሲቲን ያስተናግዳል።

አርሰናል በ24 ነጥብ አንደኛ፣  ሁል ሲቲ በ11 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዘዋል።

መድፈኞቹ ካሸነፉ የሊጉን መሪነታቸውን ያጠናክራሉ።

ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ሁል ሲቲ  ወደ አሸናፊነት የመመለስ ከባድ የቤት ስራ ይጠብቀዋል። 

በሌላኛው መርሃ ግብር  ኖቲንግሃም ፎረስት ከማንችስተር ሲቲ  ምሽት 2 ሰዓት ከ30  ላይ በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።




ኖቲንግሃም ፎረስት በስድስት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።  ቡድኑ ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

ማንችስተር ሲቲ በ21 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።  ሰማያዊዎቹ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

ሲቲ በዋንጫ ፉክክሩ  ለመቀጠል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ወሳኝ ነው። ኖቲንግሃም ፎረስትም ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይፋለማል።

ሊድስ ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ፣ ፉልሃም ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም