የመደመር እሳቤ ማሕበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት አካታች የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምኅዳር በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ነው- ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ - ኢዜአ አማርኛ
የመደመር እሳቤ ማሕበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት አካታች የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምኅዳር በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ነው- ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር እሳቤ ማሕበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት አካታች የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምኅዳር በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ።
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴክተሩን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ጉባኤ እያካሄደ ነው።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት፤ ባለፉት ዓመታት በዜጎች ሕይወት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
በሰው ተኮር ልማት የተመዘገቡ አስደማሚ ለውጦችም በሴቶች፣ ወጣቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና ልዩ ልዩ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ይህም ማኅበራዊ ፍትሕን በማንገስ በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ያስቻለ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ተናግረዋል።
የመደመር እሳቤም ማኅበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት አካታች የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምኅዳር በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይም በመደመር መንግሥት የተመዘገቡ ስኬቶችን መሰረት በማድረግ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መቀረጹን አብራርተዋል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤም ስትራቴጂክ ዕቅዱ ላይ ግብዓት ማሰባሰብና የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል።