ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር በሲዳማ ቡና እና ይርጋጨፌ ቡና መካከል ይደረጋል።

ጨዋታው ከቀኑ 10 ሰዓት በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ይካሄዳል።

ሲዳማ ቡና ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃ ይዟል።

ቡድኑ በሊጉ ባደረጋቸው ጨዋታዎች በባህር ዳር ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሽንፈት አስተናግዷል።

ተጋጣሚው ይርጋጨፌ ቡና በአንድ ነጥብ  12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።




እስከ አሁን ባከናወናቸው ሁለት ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽንፈት ሲያስተናግድ ከሃዋሳ ከተማ ጋር አቻ ተለያይቷል።

ሁለቱም ቡድኖች በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት እስከ ነገ ይቆያል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስድስት ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እጸነት ግርማ በሶስት ግቦች እየመራች ነው።




ማርታ ወልዴ (ሸገር ከተማ)፣ ፍጹም ፈለሃ (ጉለሌ ክፍለ ከተማ) ፣ አልማዝ ግርማይ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ቃልኪዳን ዘላለም (ይርጋጨፌ ቡና) እና ቤተልሄም ታምሩ (ሀዋሳ ከተማ) በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ይከተላሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም