ቀጥታ፡

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አስጀመሩ

አርባምንጭ፣ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ)፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የክልሉን  የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አስጀመሩ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጋሞ ዞን ተካሂዷል።


 

የማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ  "የውሃ ፀጋችንን አሟጠን በመጠቀም ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀ ግብርናን እውን ለማድረግ እንሠራለን" በሚል መሪ ሃሳብ  ነው፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ የክልል፣ የጋሞ ዞንና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።


 

ርዕሰ መስተዳድሩ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሉሲ እርሻ ልማት ድርጅት እየለማ የሚገኝ የማንጎ ማሳንም ጎብኝተዋል፡፡


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም