ኤቨርተን ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ኤቨርተን ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ኤቨርተን ኮቨንተሪ ሲቲን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲዬርኖ ባሪ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኪርናን ዴውስበሪ-ሆል ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ያን ግቦሆ የኮቨንተሪ ሲቲን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ኤቨርተን በ16 ነጥብ ደረጃውን ከሰባተኛ ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድላቸውን አሳክተዋል።
በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኮቨንተሪ ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በ11ኛ ሳምንት ኤቨርተን ከብሬንትፎርድ እና ኮቨንተሪ ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ ይጫወታሉ።