ቀጥታ፡

የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 27/2019(ኢዜአ)፦የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ በወታደራዊ ሙዝየም ዘርፍ የልምድ እና የተሞክሮ ልውውጥ ማድረግን አላማው ያደረገ ነው።

ኤክስፐርቶቹ አጠቃላይ የሙዚየሙን አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ሊገነባ ስለታቀደው ዘመናዊ ወታደራዊ ሙዚየም ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

‎‎ጎብኚዎቹ በበኩላቸው፣በኒጀር ሊገነባ ስለታሰበው ወታደራዊ ሙዚየም ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ጉብኝቱም ቀጣይ ለሚሰሩት ስራ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንላቸው ገልጸዋል።


 

‎‎በኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየም የወታደራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጽሐፍት መምሪያ ሀላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ ታደሰ ጎብኚዎቹ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ጠቁመው ቀጣይ በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ላይም መወያየታቸውን ተናግረዋል።

‎‎ጉብኝቱ ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ታሪክ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋላቸው ጠቁመዋል።

የኤክፐርት ቡድኑ መሪው ሲንየር ኮሎኔል ሀምዱ ድጂቦ፤ በኒጀር ለሚገነባው ወታደራዊ ሙዚየም ስራም ትልቅ ልምድ እና ተሞክሮን መቅሰማቸውን ገልፀዋል።

አክለውም፣ ቀጣይ ከሙዚየሙ ጋር በርካታ ስራዎችን በጋራ እንደሚሰሩ መግለፃቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል፡፡።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም