ኤቨርተን ከኮቨንተሪ ሲቲ ፣ የ10ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
ኤቨርተን ከኮቨንተሪ ሲቲ ፣ የ10ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።
ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ኤቨርተን ከኮቨንተሪ ሲቲ በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባለሜዳው ኤቨርተን በ13 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል።
ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ19ኛ ጊዜ ነው።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 18 ጨዋታዎች ኮቨንተሪ ሲቲ ሰባት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ኤቨርተን ሶስቱን ሲያሸንፍ በቀሪ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ኮቨንተሪ በ18ቱ ጨዋታዎች ላይ 22 ግቦችን ሲያስቆጥር ኤቨርተን 15 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ በ2001 ነው። በወቅቱ ኤቨርተን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ሁለቱ ክለቦች ከ25 ዓመታት በኋላ ዳግም በሊጉ ይገናኛሉ።
ኮቨንተሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱ ይታወሳል።
የ44 ዓመቱ ስቱዋርት አትዌል ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት እስከ ጥቅምት 29 2019 ዓ.ም ይቆያል።