ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን የልማት ተሞክሮን እያጋራች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን የልማት ተሞክሮን እያጋራች ነው
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ የ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች የልማት ተሞክሮዋን እያጋራች ነው።
የ2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የለሙትን የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ጎብኝተዋል።
እንዲሁም የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ፣ እና ሌሎች በከተማዋ እየለሙ ያሉ ሰው ተኮር መሠረተ ልማቶችን በመጎብኘት የከተማዋን የልማት ለውጦችና የከተማ ማደስ ተሞክሮዎችን መጎብኘታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ይህ ጉብኝት አዲስ አበባ በከተማ ልማት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎች ግንባታና በዘመናዊ የከተማ አደረጃጀት ዘርፎች እያከናወነች ያለውን ሥራ ለመመልከት ዕድል እንደፈጠረላቸው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የልማት ተሞክሮ፣ የለውጥ ጉዞና የአፍሪካ ትስስር መድረክ!