ቀጥታ፡

አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2019 (ኢዜአ)፦  የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ትናንት ማምሻውን ተካሄዷል።

በፎርቹና አሬና በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ኖኒ ማዱዌኬ እና ቪክቶር ዮኮሬስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዊክቶር ኖዋክ የስላቪያን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ10  ነጥብ ሶስተኛ፣ ስላቪያ ፕራግ በአንድ ነጥብ 34ተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ አርቢ ላይፕዚግን 3 ለ 2 አሸንፏል።




በሬድ ቡል አሬና በተደረገው ጨዋታ አርሊንጎ ሀላንድ፣  ኤንዞ ፈርናንዴዝ እና የላይፕዚጉ ካስቴሎ ሉኬባ በራሱ ላይ የሲቲን ግቦች አስቆጥረዋል።

ሪድል ባኩ እና አንቶኒዮ ኑሳ የላይፕዚግን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

አርቢ ላይፕዚግ በሶስት ነጥብ 29ኛ ደረጃን ይዟል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች ኮሞ ሌንስን 9 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ረትቷል።

ፖርቶ ናፖሊን  እና ቫይኪንግ ሳባህን በተመሳሳይ 4 ለ 1 አሸንፈዋል።

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሪያል ቤቲስን እና ክለብ ብሩዥ ፒኤስቪ አይንድሆቨንን በተመሳሳይ 2 ለ 1 ረትተዋል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የአምስተኛ ዙር መርሐ ግብር  ከህዳር 15 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም