ሊቨርፑል ሽንፈት ሲያስተናግድ ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል ሽንፈት ሲያስተናግድ ሪያል ማድሪድ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ፊነርባቼ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 ረትቷል።
በሱክሩ ሳራኮግሉ በተካሄደው ጨዋታ አርቺ ብራውን፣ ሜሰን ግሪንውድ እና ቬዳት ሙርኪ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ትሬይ ንዮኒ እና አሌክሳንደር ኢሳቅ የሊቨርፑልን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ፊነርባቼ በአምስት ነጥብ 19ኛ፣ ሊቨርፑል በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ኤኢኬ አቴንስን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በኦልዊን አሬና በተደረገው ጨዋታ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ኪሊያን ምባፔ እና ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አቡባካሪ ኮይታ እና ስታቭሮስ ፒሎስ የግሪኩን ክለብ ጎሎች አስቆጥረዋል።
ሪያል ማድሪድ በ12 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ኤኢኬ አትንስ በሶስት ነጥብ 30ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።