ቀጥታ፡

የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና ለጋራ ትርክት ግንባታ ፅኑ መሰረት እያኖረ ነው

ጋምቤላ ፤ ጥቅምት 25/ 2019 (ኢዜአ ) ፦ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና ለጋራ ትርክት ግንባታ ፅኑ መሰረት እያኖረ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ይሳቅ አብርሀም ገለጹ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአሉን በማስመልከት ከጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ይሳቅ አብርሀም ጋር ቆይታ አድርጓል።

አፈ-ጉባኤው እንደገለጹት በየዓመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሀገራዊ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር መልካም እድል የፈጠረ ነው።

ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና ለጋራ ትርክት ግንባታ ፅኑ መሰረት እያኖረና የጋራ ልማትና ተጠቃሚነትን እያጠናከረ መሆኑንም ገልጸዋል።

የበዓሉ አከባበር በብዝሃነት ውስጥ ያለውን ውበት አድምቆ ከማሳየት ባለፈ የህዝቦችን የጋራ ታሪክ በማጠናክር ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲተጉ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የዘንድሮው 21ኛ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዘቦች ቀንም ይህንኑ መሰረት አድርጎ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ የአስተዳደር መወቅሮች የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በአሰባሳቢ ትርክቶች ዙሪያ ግንዛቤን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ የሚከበር መሆኑንም ጠቁመዋል።

የዘንድሮው 21ኛ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ’’በብዝሃነት የደመቀች፣ በምክክር የጸናች፣ ስልጡን ኢትዮጵያ’’ በሚል መሪ ሃሳብ በጅማ ከተማ የሚከበር መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም