ቀጥታ፡

ኢኮኖሚያችን ፈተናዎችን እንዲቋቋም፣ ቀድሞ መዘጋጀትና አማራጮችን ማስፋት የግድ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦ኢኮኖሚያችን አይበገሬ ሆኖ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን እንዲቋቋም፣ ቀድሞ መዘጋጀትና አማራጮችን ማስፋት የግድ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በባሌ ዞን የክረምት እርሻ አፈጻጸምን መመልከታቸውን አስታውቀዋል።

በዘንድሮው ክረምት ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሥጋት የነበረ ቢሆንም በመንግሥትና በሕዝብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መልካም የሚባል አፈጻጸም ተመዝግቧል ብለዋል። 


 

ኢኮኖሚያችን አይበገሬ ሆኖ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን እንዲቋቋም፣ ቀድሞ መዘጋጀትና አማራጮችን ማስፋት የግድ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም