ኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የምትለካበትን አዲስ ስሌት ይፋ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የምትለካበትን አዲስ ስሌት ይፋ አደረገች
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ መለካት የሚያስችል አዲስ ስሌት በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) አንድ ሀገር በተወሰነ ጊዜ፣ በአብዛኛው በአንድ ዓመት በሀገር ውስጥ ያመረታቸውን ሁሉንም የመጨረሻ ሸቀጦች እና አገልግሎቶች በገበያ ዋጋ የሚለካ ኢኮኖሚያዊ መለኪያ ነው።
በዚህ መለኪያ ውስጥ የቤተሰቦች ፍጆታ፣ የንግድ ተቋማት እና የግል ባለሀብቶች ኢንቨስትመንት፣ የመንግሥት ወጪ እንዲሁም ከወጪ ንግድ የሚገኘው የተጣራ ውጤት ተደምረው ይሰላሉ።
ኢትዮጵያም ከፈረንጆቹ 1960 ጀምሮ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መረጃዋን በይፋ ስታሳውቅ ቆይታለች።
ሆኖም እስካሁን ሥራ ላይ የነበረው የ2008 ዓ.ም የመነሻ ዓመት ስሌት በኢኮኖሚው የተፈጠሩ አዳዲስ ለውጦችን እና የዘርፎችን መስፋፋት በበቂ ሁኔታ የሚያንፀባርቁ አለመሆናቸው ተገልጿል።