በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች - ኢዜአ አማርኛ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ማምሻውን ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የባለፈው ዓመት የፍጻሜ ተፋላሚ አርሰናል ከስላቪያ ፕራግ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በፎርቹና አሬና ይጫወታል።
አርሰናል እስከ አሁን ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሰባት ነጥብ በማግኘት ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
ባለሜዳው ስላቪያ ፕራግ በአንድ ነጥብ 32ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት አግኝቷል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ኤኢኬ አቴንስ ከሪያል ማድሪድ በአግያ ሶፊያ ስታዲየም ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
የ15 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። የግሪኩ ክለብ በሶስት ነጥብ 27ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፊነርባቼ ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በሱርኩ ሳራኮግሉ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል።
የቱርኪዬው ክለብ በሁለት ነጥብ 31ኛ ደረጃን ይዟል።
የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በዘጠኝ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፊነርባቼ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ሊቨርፑል በመልካም ጅማሮው ለመቀጠል ይፋለማል።
ምሽት አምስት ሰዓት ላይ አርቢ ላይፕዚግ ከማንችስተር ሲቲ በሬድ ቡል አሬና ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
አርቢ ላይፕዚግ በሶስት ነጥብ 29ኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ በስድስት ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የጀርመኑ ክለብ በሶስተኛ ሳምንት በሪያል ማድሪድ የ4 ለ 1 ሽንፈት ሲያስተናግድ ማንችስተር ሲቲ ኤኢኬ አቴንስን 5 ለ 1 ረትቷል።
ጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ተከታታይ ድሉ ለማስመዝገብ በአንጻሩ አርቢ ላይፕዚግ የአሸናፊነት መንገዱን ለማግኘት የሚያደርጉት ነው።
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከሪያል ቤቲስ፣ ፖርቶ ከናፖሊ፣ ሌንስ ከኮሞ፣ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከክለብ ብሩዥ እና ቫይኪንግ ከሳባህ በተመሳሳይ ምሽት አምስት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።