ፒኤስጂ፣ ባርሴሎና፣ ባየር ሙኒክ እና ማንችስተር ዩናይትድ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
ፒኤስጂ፣ ባርሴሎና፣ ባየር ሙኒክ እና ማንችስተር ዩናይትድ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ትናንት ማምሻውን ተደርገዋል።
በዴላ ሴራሚካ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፒኤስጂ ቪያሪያልን 6 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
ፋቢያን ሩዊዝ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዴዚሬ ዱዌ፣ ጆአኦ ኔቬስ፣ ሴኒ ማዩሉ እና ዴቪድ ቦሊ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የወቅቱ ሻምፒዮን ፒኤስጂ በ12 ነጥብ በሊግ ምዕራፍ ውድድሩ መሪነት ቀጥሏል።
ቪያሪያል በሶስት ነጥብ 29ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ባርሴሎና አስቶንቪላን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ራፊንሃ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አገናኝቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና እና አስቶንቪላ በተመሳሳይ ዘጠኝ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ባየር ሙኒክ አትሌቲኮ ማድሪድን 2 ለ 0 ረትቷል።
ሌናርት ካርል እና ኮንራድ ላይመር ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ባየር ሙኒክ በስምንት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ሲይዝ አትሌቲኮ ማድሪድ በአራት ነጥብ 22ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከ2 ለ 0 መመራት ተነስቶ 3 ለ 2 አሸንፏል።
በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማቲያስ ሱሌ በጨዋታ እና ዶንየል ማለን በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሩት ግብ ሮማ ለእረፍት 2 ለ 0 እየመራ ወጥቷል።
በሁለተኛው አጋማሽ ሚቲያስ ኩንሃ ሁለት ግቦችን፣ አምበሉ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በፍጹም ቅጣት ምት ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሮ ዩናይትድ አሸናፊ ሆኗል።
ኩንሃ ግቦቹን ያስቆጠረው በ83ኛው እና በ86ኛ ደቂቃ ላይ ነው። ተጫዋቹ በ91ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ወጥቷል።
ይሆን ተከትሎም ማንችስተር ዩናይትድ ከዘጠኝ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። በስድስት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።
ሮማ በአራት ነጥብ 19ኛ ደረጃ
ላይ ይገኛል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ኢንተር ሚላን ፌይኖርድን 3 ለ 0 እና ላስክ ስሎቫን ብራቲስላቫን 4 ለ 0 አሸንፈዋል።
ቦዶ ግሊምት ከሊል ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።