ጋላታሳራይ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጋላታሳራይ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ማምሻውን ተጀምሯል።
በራምስ ፓርክ በተካሄደው ጨዋታ ጋላታሳራይ አሌክሲ ባትራኮቭ ባስቆጠራቸው ጎሎች ስቱትጋርትን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ጋላታሳራይ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ስቱትጋርት የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ስፖርቲንግ ሊዝበን ሻካታር ዶኔስክን 1 ለ 0 ረትቷል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ኢሳ ዱምቢያ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ስፖርቲንግ ሶስተኛ የሻምፒዮንስ ሊግ ድሉን ሲያሳካ የዩክሬኑ ክለብ ለሁለተኛ ጊዜ ተሸንፏል።