ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድን፤ የአምስተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ መድን መካከል ዛሬ ይካሄዳል።

ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘንድሮ በሊጉ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ስምንት ነጥብ በማግኘት አራተኛ ደረጃን ይዟል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ኢትዮጵያ መድን በአራት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

ሁለቱም ክለቦች በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ድል አልቀናቸውም።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁለቱ ጨዋታዎች አቻ ሲወጣ፣ መድን በበኩሉ በአንዱ ተሸንፎ በቀሪው ጨዋታ አቻ ተለያይቷል።

ሁለቱ ክለቦች በ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት ባደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ አንድ ጊዜ አሸንፈዋል።

የዛሬው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም