ቀጥታ፡

አርሰናል ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር አርሰናል ሊቨርፑል አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ካይ ሃቫርትዝ በ16ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

ዴክላን ራያስ ለግብ የሆነውን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።

በጨዋታው አርሰናል የተሻሉ የግብ እድሎች ፈጥሯል።

ባለሜዳው ሊቨርፑል በጨዋታው የነበረውን የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።

አርሰናል በሊጉ አንፊልድ ሮድ ላይ ከ14 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በ24 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከማንችስተር ሲቲ ተረክቧል።

ከሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነትም ሶስት ሆኗል።

ሊቨርፑል በ15 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም