በተጠባቂው መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና መቻል ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ጨዋታው ትናንት ማምሻውን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በአንድ ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች ይቀሩታል።
መቻል በ10 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ በቢላል ገመዳ ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በመርታት የሊጉን የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል።
ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0፣ ሀዋሳ ከተማ ጋሞ ጨንቻን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድን ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።