በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ክፍለ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የምስራች ላቀው፣ እጸገነት ግርማ እና ሰናይት ቦጋለ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
መታሰቢያ ኃያሉ የቦሌ ክፍለ ከተማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስድስት ነጥብ በሊጉ መሪነት ቀጥሏል።
ቦሌ ክፍለ ከተማ በሶስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እጸገነት ግርማ በሶስት ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መምራት ጀምራለች።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከልን 2 ለ 0፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 2 እና ባህር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ ሁለተኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 28 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።