ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ዛሬ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግብ ቢላል ገመዳ በ80ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተካሄደ ሌላ ጨዋታ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ጋሞ ጨንቻን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በጨዋታው ቃልኪዳን ዘላለም የሀዋሳ ከተማን ግቦች ሲያስቆጥር የትምጌታ ታደሰ የጋሞ ጨንቻን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።