ቀጥታ፡

ልማት ሰውን ማዕከል ሲያደርግ፤ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ መንደር ሌላኛው ማሳያ ነው

እውነተኛ ልማት የሚለካው የሰዎችን ሕይወት በምን ያህል ደረጃ እንደቀየረ በሚያሳየው ውጤት ነው፤ ይህም በከተማችን በተጨባጭ እየታየ ይገኛል።

አዲስ አበባ ለልማት ፕሮጀክቶች መሬት ስታውል የዜጎቿን መብት፣ ጥቅምና የኑሮ ሁኔታ በማክበር ልማትን ከሰው ሕይወት ጋር አስተሳስራ እየሠራች ነው።

የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደርም የዚህ አካሄድ ጉልህ ማሳያ ነው።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ለሀገራዊ የቴክኖሎጂና ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ አቅም የሚፈጥር ፕሮጀክት ቢሆንም፣ የልማቱ ተነሺዎች የነበራቸው የኑሮ ዘይቤና ማኅበራዊ ትስስር እንዳይጎዳ ልዩ ትኩረት ተደርጎለታል።


 

በዚህም 17 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የተገነባው የሹቡ ኤጀርሳ መንደር ለነዋሪዎች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ከማቅረብ ባለፈ፣ የወተት ላም ማርቢያ ሼዶችን፣ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያን፣ የንግድ ሱቆችን፣ የምርት መሸጫ መጋዘንን፣ ወፍጮዎችንና ሌሎች አገልግሎቶችን አካቷል።

ከዚህም በላይ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ አዳራሽ በማካተት የቤተሰብን ሕይወት በሁሉም ዘርፍ ለማሻሻል ተሠርቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም