ቀጥታ፡

በደርቢው ጨዋታ ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ በጣልያን ሴሪአ የ10ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ኢንተር ሚላንን 3 ለ 1 ረትቷል።

ትናንት ማምሻውን በሳንሲሮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክሪስቲያን ፑሊሲች፣ አድሪያን ራቢዮት እና ዲያጎ ሞሬራ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አሌሳንድሮ ባስቶኒ የኢንተር ሚላንን ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው ኤሲ ሚላን ያደረጋቸውን ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ወደ ግብ ቀይሯል።

በአንጻሩ ኢንተር ሚላን የግብ እድሎቹን በሚገባ አልተጠቀመም።

ድሉን ተከትሎ ኤሲ ሚላን በ21 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢንተር ሚላን በ25 ነጥብ ከነበረበት አንደኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ዝቅ ብሏል።

የሊጉን መሪነትም ለላዚዮ አስረክቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም