ቀጥታ፡

ቶተንሃም ሆትስፐርስ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርቺ ግሬይ እና ጃን ፖል ቫንሄከ  ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የክሪስታል ፓላሱ አጥቂ ጂን-ፍሊፕ ማቴታ በ13ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

የተጫዋቹ መውጣት በክሪስታል ፓላስ ጨዋታ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል።

ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ12 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ክሪስታል ፓላስ በሰባት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌላኛው መርሐ ግብር አስቶንቪላ ከፉልሃም አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በቪላ ፓርክ በተካሄደው ጨዋታ ኒኮላስ ጃክሰን የአስቶንቪላን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የአስቶንቪላው ግብ ጠባቂ ዛዮን ሱዙኪ በራሱ ላይ የፉልሃምን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ አስቶንቪላ በ12 ነጥብ ዘጠነኛ፣  ፉልሃም በዘጠኝ ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም