ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውጤቶች

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ይርጋጨፌ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ሶስት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በሃዋሰ አርቴፊሻል ሜዳ በተደረገው ጨዋታ ቃልኪዳን ዘላለም ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ቤተልሄም ፈርኦን ቀሪዋን ጎል ለይርጋጨፌ አስቆጥራለች።

ስራ ይርዳው፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ እና ቤተልሄም ታምሩ የሃዋሳ ከተማን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ሸገር ከተማ ከአዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተከናወነው መርሐ ግብር ማያ አስራት ለሸገር ከተማ፣ ምስር ኢብራሂም ለአዳማ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም