ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ በብራይተን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብራይተን ማንችስተር ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሲን አያሪ በ11ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል።

ማንችስተር ሲቲ በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም ሊሳካላት አልቻለም።

ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ በ21 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። ከተከታዩ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ከፍ የማድረግ እድል አልተጠቀመበትም።

የወቅቱ ሻምፒዮን አርሰናል ነገ ሊቨርፑልን ካሸነፈ ወይም አቻ ከወጣ የሊጉን መሪነት ከሲቲ ይረከባል።

ወሳኝ ድል የተቀዳጀው ብራይተን በ19 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች ብሬንትፎርድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0፣ ኮቨንተሪ ሲቲ ሰንደርላንድን 3 ለ 1 እና ቦርንማውዝ ሊድስ ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

ሁል ሲቲ ከኤፕስዊች ታውን ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከክሪስታል ፓላስ፣ አስቶንቪላ ከፉልሃም ምሽት አምስት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም