በተጠባቂው መርሐ ግብር ቼልሲ ማንችስተር ዩናይትድን አሸንፏል - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው መርሐ ግብር ቼልሲ ማንችስተር ዩናይትድን አሸንፏል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ ቼልሲ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 0 ረትቷል።
በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጎሎቹን ሞርጋን ሮጀርስ እና ኮል ፓልመር በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።
በጨዋታው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ16 ነጥብ አራተኛ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች እንዲሁም በሁሉም ውድድሮች ባለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ከድል በመራቅ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።