ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ ከባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በባህር ዳር ኢንተርሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ናይጄሪያዊው ጄሮም ፍሊፕ እና ታምራት እያሱ ለፋሲል ከነማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አንተነህ ተፈራ የባህር ዳር ከተማን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ፋሲል ከነማ በሶስት ነጥብ 14ኛ፣ ባህር ዳር ከተማ በሰባት ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ አንድ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አላቸው።

የባህር ዳር ከተማው አንተነህ ተፈራ በአምስት ጎሎች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መምራት ተጀምሯል።




በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥብ 12ኛ፣ አዳማ ከተማ በስድስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም