ቀጥታ፡

ሀላባ ከተማ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ሀላባ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሀላባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናትናኤል ሰለሞን እና ፍሬው ሰለሞን ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ደስታ ዋሚሾ በፍጹም ቅጣት ምት የሀዲያ ሆሳዕናን ጎል አስቆጥሯል።

በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ በስምንት ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።

በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና በአራት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

ሀዲያ ሆሳዕና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል።

በስድስተኛ ሳምንት ሀላባ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም