ነገሌ አርሲ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ዳግም ወደ ሊጉ መሪነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ነገሌ አርሲ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ዳግም ወደ ሊጉ መሪነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ሸገር ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሀቢብ ከማል እና ጋናዊው ኮሊንስ ኮፊ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ዳዊት ካሳው የሸገር ከተማን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ጨዋታውን ያሸነፈው ነገሌ አርሲ በ11 ነጥብ ደረጃውን ከሁለተኛ ወደ አንደኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በአምስት ነጥብ ከነበረበት ሰባተኛ ደረጃ ወደ ዘጠነኛ ዝቅ ብሏል።
በስድስተኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ ከጋሞ ጨንቻ፣ ሸገር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።