ቀጥታ፡

የትራንስፖርት አገልግሎታችንን ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎታችንን የበለጠ ፈጣን፣ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ዛሬ ሥራ አስጀምረዋል፡፡

ይህንን አስመልክተው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፡- ይህ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ርምጃ ሲሆን፣ የትራንስፖርት ወጪንና የአየር ብክለትን ለመቀነስ፣ የዜጎችን ጊዜ ለመቆጠብና የሀገር ውስጥ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ ተጨባጭ የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው ሲሉ ገልጸዋል።


 

በራሳችን አቅም የተጀመረው ይህ ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባዋ ፤ በቅርቡም 400 አዳዲስ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ አውቶብሶች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።

ዓላማችን ወጪ ቆጣቢ፣ አካባቢን የሚጠብቅ፣ ፈጣንና ተደራሽ የሕዝብ ትራንስፖርት በመገንባት የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ማሻሻል ነው ሲሉም ገልጸዋል።


 

ለዚህም የትራንስፖርት አገልግሎታችንን የበለጠ ፈጣን፣ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በራሳችን አቅም፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም