ቀጥታ፡

 የአዲስ አበባን እድገት የሚመጥን የአደጋ መከላከል አቅም ተገንብቷል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባን እድገት የሚመጥን የአደጋ መከላከል አቅም መገንባቱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን ቶላ ገለፁ፡፡

ኮሚሽኑ ከፖላንድ ዓለም አቀፍ እርዳታ ማዕከል (PCPM) እና ከዓለም አቀፍ የገጠር ማሻሻያ ኢንስቲትዩት (IIRR) ጋር በመተባበር ያስገነባውን ዘመናዊ የተግባር መለማመጃ ማሰልጠኛ ማዕከል እና የሰልጣኞች ምረቃ መርሃግብር አካሂዷል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ጥላሁን ቶላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ አዲስ አበባ እያስመዘገበች ካለው ፈጣን የከፍታ ሕንፃዎች ግንባታና ዕድገት አንጻር የደህንነት ጉዳይ ወሳኝ ነው።

ሰልጣኞቹ በከፍተኛ ቦታዎች ላይ ለሚከሰቱ አደጋዎች የሚደረግ ማዳን፣ የቅድመ-ሆስፒታል ሕክምና እና ከእሳት አደጋ የማዳን ስልጠና መውሰዳቸውንም ገልጸዋል።

አዲሱ ማዕከልና ሲሙሌተር የአደጋ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የሰው ሕይወትና ንብረትን ለማዳን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፖላንድ ኤምባሲ ፀሐፊ ማቴኡሽ ለምፕኮቭስኪ በበኩላቸው፣ በፕሮጀክቱ የእሳት አደጋ መከላከያና ማዳኛ መሳሪያዎች መቅረባቸውን፣ የአምቡላንስ አገልግሎቶች በሕክምና ቁሳቁስ መሟላታቸውን እና የሕክምና ባለሙያዎች በቅድመ-ሆስፒታል ድንገተኛ እንክብካቤ ላይ ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም