ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ሹም ተምቤን ፓርቲ" ሕጋዊ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ ሰጠ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ሹም ተምቤን ፓርቲ (ሹ.ተ.ፓ)" ሕጋዊ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለ“ሹም ተምቤን ፓርቲ" ሕጋዊ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት መስጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም