ቀጥታ፡

በኢንተርፖል ዋና ፀሐፊ ቫልደሲ ኡርኪዛ የተመራ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦ በዓለም አቀፍ የፖሊስ ሕብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) ዋና ፀሐፊ ቫልደሲ ኡርኪዛ የተመራ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ታምራት ሙሉጌታ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገዋል።


 

ልዑካኑ በቆይታቸው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኢንተርፖል አባል ሀገራት የሕግ አስከባሪዎች ደረጃውን የጠበቀና ከፍተኛ ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ከሚታወቀው የኢንተርፖል ግሎባል አካዳሚ ጋር የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም