ቀጥታ፡

ኤቨርተን በካራባኦ ካፕ ለሩብ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2019 (ኢዜአ)፦ በካራባኦ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጀምስ ጋርነር፣ ሄይደን ሀክኒይ እና ቲዬርኖ ባሪ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዳን በርን የኒውካስትል ዩናይትድን የማስተዛዘኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል።

ባለሜዳው ኤቨርተን ያገኛቸውን የግብ እድሎች በሚገባ ተጠቅሟል።

ኒውካስትል የግብ አጋጣሚዎቹን መጠቀም አለመቻሉ ዋጋ አስከፍሎታል።

ኤቨርተን  በካራባኦ ካፕ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፈ የመጨረሻው ክለብ ሆኗል።

ጨዋታውን ተከትሎ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ተጠናቋል።

ሊቨርፑል ከቦርንማውዝ፣ ማንችስተር ሲቲ ከብራድፎርድ ሲቲ፣ ክሪስታል ፓላስ ከሰንደርላንድ እና ኤቨርተን ከፍሊትውድ ታውን በሩብ ፍጻሜው ይጫወታሉ።

የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር በታህሳስ ወር 2019 ዓ.ም መጀመሪያ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም