ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሩሲያው የዜና አገልግሎት ታስ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ከሩሲያው የዜና አገልግሎት ታስ (TASS) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ የተፈረመው ከሩሲያ-አፍሪካ የሚዲያ ፎረም ጎን ለጎን ነው።

ስምምነቱ በሁለቱ የዜና አገልግሎቶች መካከል የመረጃ ልውውጥ ማድረግን፣ የሰራተኞችን አቅም መገንባትና የስልጠና ፕሮግራሞችን ማመቻቸትን እንዲሁም የሰራተኞች የእርስ በእርስ ጉብኝቶችን ማድረግን ያካተተ ነው።

የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ እና የታስ የዜና ወኪል ዋና ዳይሬክተር አንድሬ ኮንድራሾቭ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም