ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ  ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ሀሳቦች

. የኢትዮጵያና የሩሲያ ወዳጅነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀ በመሆኑ፣ ከአድዋ ጦርነት በኋላ የሩሲያ ቀይ መስቀል ያደረገውን የሕክምና እገዛና የመጽሐፍ ትርጉም አርአያ በማድረግ የአሁኑም ስምምነቶች ወደ ተጨባጭ ውጤት መለወጥ አለባቸው።
 
. የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ መነሻ ሉዓላዊነትና የራስን የመወሰን አቅም ማሳደግ ሲሆን፣ የሀገራት በምርትና ሳይንስ በጋራ ማደግ ሙሉ ጥንካሬን ይፈጥራል።
 
. የዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና ዘላቂ የግብርና ኢኮኖሚ መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በመሆኑ፣ ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ትብብር በግብርና ማሽነሪዎች አቅርቦትና ምርት ማቀናበሪያ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያተኩራል።
 
. የኃይል አማራጭን ለማበልጸግ ከሩሲያ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን የኑክሌር ኃይል ማመንጫ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፤ ይህም የዓለም አቀፍ የኒውክሌር ኤጀንሲን መስፈርት የተከተለና የምግብ ብክነትን ለመቀነስ እንዲሁም የካንሰር ሕክምናን ለማስፋፋት ይውላል።
 
. የአፍሪካ ተመራማሪዎች በራሳቸው ቋንቋ መሣሪያዎችን መፍጠር አለባቸው፤ በአዳማ ከተማ እየተገነባ ባለው የአርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ዩኒቨርሲቲም የሩሲያ ተቋማት አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።
 
. የሩሲያ ኩባንያዎች በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች ውስጥ በመድኃኒትና ማሽነሪ ዘርፍ የጋራ ኩባንያዎችን መመስረት ይኖርባቸዋል።
 
. በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚከናወኑ የንግድና ኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ቀላል፣ ፈጣንና አነስተኛ ወጪ የሚያስወጡ ለማድረግ የክፍያ መስመሮችን (Payment channels) ማቀናጀት ይገባል።

. የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሣሪያዎች የአፍሪካውያንን መረጃ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉ የሀገሪቱ ተቋማት ራሳቸው የመወሰን መብት ሊኖራቸው ይገባል።
 
.በዩኒቨርሲቲዎችና በምርምር ተቋማት የሚመነጩ አዳዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በወረቀት ላይ ሳይቀሩ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ ምርት፣ ኢንዱስትሪ እና ንግድ ውጤቶች  መቀየር ይኖርባቸዋል።
 
. በሚቀጥለው ጊዜ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ወደ አፍሪካ ሲመጣ የአፍሪካ ህብረት መዲና የሆነችው አዲስ አበባ  ለማስተናገድ  ዝግጁ ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም