ቀጥታ፡

በሸገር ከተማ በምግብ ራስን የመቻል ዕቅድን ለማሳካት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል

ሸገር, ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ):- በሸገር ከተማ በምግብ ራስን የመቻል ዕቅድን ለማሳካት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል።

የሸገር ከተማ በኦሮሚያ ክልል ፈጣን የከተማ ዕድገትና የህዝብ ቁጥር መጨመር ከሚታይባቸው ዋና ዋና አካባቢዎች አንዱ ነው። 

ከተማው በከፊል የከተማ እና በከፊል የገጠር ባህሪ ያላቸውን አካባቢዎች አካቶ የያዘ በመሆኑ፣ የግብርና ልማትን ከከተማ ዕድገት ጋር አስተሳስሮ መምራት አስፈላጊ ሆኗል። 


 

የህዝቡን የምግብ ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላትና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በምግብ ራስን የመቻል አገራዊና ክልላዊ ራዕይ አካል የሆኑ የተለያዩ የግብርና ልማት ኢንሼቲቮች ተዘርግተዋል።


 

በዛሬው እለትም በከተማው መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና አርሶ አደሮች በተገኙበት የተለያዩ የግብርና ልማትና የቤተሰብ ብልጽግና ኢንሼቲቮች የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

በመስክ ምልከታው ላይ የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የሸገር ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ፣ እንዲሁም የከተማውና የክፍለ ከተማው አመራሮች ተገኝተዋል።


 

በመስክ ምልከታው የዶሮ እርባታ፣ የገብስና ስንዴ የኩታ ገጠም ልማት፣ የወተት ላም እርባታ፣ የሙዝ ክላስተር እና የተመራጭ የገብስ ዘር ማባዛት ኢንሼቲቮች ተጎብኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም